Graduation Magazine
መንገድ፤ የአንድን አካባቢ ብሎም የከተማና የሀገርን ሁለንተናዊ እድገት ለማፋጠን ቁልፍ ድርሻ ከሚያበረክቱ
መሠረተ-ልማቶች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው፡፡ ሁሉም ዓይነት መሠረተ-ልማቶች ለተቀናጀና ሁሉን አቀፍ
ዘመናዊ እድገት አስፈላጊ መሆናቸው አጠያያቂ ባይሆንም፤ ሌሎች የመሠረተ-ልማት አቅርቦቶች በፍጥነትና
በስፋት እንዲዳረሱ የመንገድ ግንባታ በእጅጉ ያስፈልጋል፡፡